አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በትምህርት፣ በጤና እና በወጣት ልማት ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው:: ድርጅታችን ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች 02 (ሁለት) የመፀዳጃ ቤቶችን ማስገንባት ይፈልጋል::
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በትምህርት፣ በጤና እና በወጣት ልማት ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው::
ድርጅታችን ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች 02 (ሁለት) የመፀዳጃ ቤቶችን ማስገንባት ይፈልጋል::
በመሆኑም:-
-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንከ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም /Tin Number/፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው ወይም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ነፃ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍለ-ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ /መረጃ/ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው በመግዛት የማቴሪያል ወጪ ጨምሮ የምትሰሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል::
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በ8ኛው የሥራ ቀን በ3:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል:: ስምንተኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ይሆናል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-2-76-35-39/ 011-2-13-18-29/ 09-96-23-09-27
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት
