Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ1. ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111 71 22 00
  • Website
  • Deadline16 Jan 2025, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Maintenance And Repair

የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግሥት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ1. ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም

 

የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግሥት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የሰራተኛ ደንብ ልብስ

ሎት 2 የቢሮ የጽሕፈት አላቂ እቃዎች

ሎት 3 የህትመት ስራዎች

ሎት 4 አላቂ የጽዳት እቃዎች

ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች

ሎት 6 የህክምና አላቂ እቃዎች

ሎት 7 ቋሚ ፈርኒቸር እቃዎች

ሎት 8 የተለያዩ ጥገና

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት አለባቸው፡፡

  1. በሞያው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር በመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ።
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎት ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል ለቋሚ እቃ በሎት ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር/ እና ለሌሎች አላቂ እቃዎች በየሎት ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በክፍል አራት፣ ስድስት እና ዘጠኝ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በየሎት የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 9 ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ወዛደር የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ከተለየበት ቀን አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  12. በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ሰነዱ በነጻ የሚወሰዱ ይሆናል፡፡ በማያመርቱት ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  14. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. ተጫራቾች ባሸነፉበት የእቃ ርከከብ የሚደረግበት ሰዓት 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ቴክኒከ ኮሚቴዎች መኖራቸውን አረጋግጦ ማምጣት አለበት፡፡
  16. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ልዩ ቦታ ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ

በስልከ ቁጥር፡- 0111 71 22 00 እና 0111-55-07-24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ1. ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender