የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት 18-02B ማዕከል ውስጥ ለሚገነባቸው ግንባታዎች የሚውል የፎርምወርክ እና ፈረሳ የጉልበት ስራ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ፕሮ/18-02B/ማስ/0320/17
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በመከላከያ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት 18-02B ማዕከል ውስጥ ለሚገነባቸው ግንባታዎች የሚውል የፎርምወርክ እና ፈረሳ የጉልበት ስራ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆሬ አደባባይ በሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18- 02B) አቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በ20ኛው ቀን ከሠዓት በ8፡00 ሠዓት ጨረታው ተዘግቶ 8፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም በዕለቱ የሌጋል ዶክመንት የሚከፈት ሲሆን የቴክኒካል ግምገማውን ያለፉት ደግሞ ፋይናንሻል የሚከፈትበትን ቀን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ
2. የታደሠ የምዝገባ የንግድ ሥራ ፈቃድ
3. የተጨማሪ ቫት ተጠቃሚ መሆናችሁን የሚገልፅ የቫት ሰርተፊኬት
4. የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. የሚቀርቡትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
* ፕሮጀክቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ፡- መከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት 18-02B ቆሬ አደባባይ
ለበለጠ መረጃ :- 011-8-72-11-74 ወይም 0942-06-33-02
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቆሬ አቅም ግንባታ ኮሌጅ ፕሮጀክት 18-02B
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
