በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የአደጋ መከላከያ የሴፍቲ ጫማ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
የአደጋ መከላከያ የሴፍቲ ጫማ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር /ኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/15/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የአደጋ መከላከያ የሴፍቲ ጫማ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ማለትም ፡-
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ብር /ሠላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታች ላይ ያልተመሰረት የ60 ቀናት የባንክ ዋ ዋስትና (Unconditional bid bond guarantees) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በደርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከሲ.አር.ዲ.ኤ አጠገብ
ስልክ ቁጥር ፡- 09 21 02 25 81/0114-62-14-57
የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት
