የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለባህርዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውል PSupply and fix Fuel Pump ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/02/2025
የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለባህርዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የSupply and fix Fuel Pump ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply and Fix Fuel Pump |
የባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/SF/02/2025
|
ጥር 16/2017 ዓ.ም 4:15
|
ጥር 16/2017 ዓ.ም 4:30 |
50,000.00 |
ስለሆነ ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ የታደሰ ታክስ ከሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditiona Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት ሞዴል/ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce.gov.com/www.et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
