በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በአስራ ሁለት ከተሞች ሊሰራ በታቀደው መሠረት Ground Control Point (GCP) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በአስራ ሁለት ከተሞች ሊሰራ በታቀደው መሠረት Ground Control Point (GCP) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ደረጃቸው GC-9 የሆኑ ፣ በ2017 በጀት ዓመት የንግድ ፈቃድ ያደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማቅረብ የሚቻሉ፣ አግባብነት ካለው መንግስታዊ ተቋም ( በፌዴራል እና በሲዳማ ክልል ) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ ስለ መሆናቸው የምዘገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን ማሰራት እና ማጠናቀቅ የሚችሉ፤
- በገባው ውሉ መሠረት ፕሮጀክት ሠርቶ ያስረከበ እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፤
- ድርጅቱ ለውድድር ያቀረበው ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ ማቅረብ እና ማመሳከር የሚችሉ፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ገር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ማስከበሪያ (Bid Security) የሚሆን ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ) ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ እና ደንብ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለስራው የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ/ፋይናንስ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሟልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ፋይናንሺያል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል ) ሁለት ሁለት ኮፒዎች ሰነድ በተለያየ ኤንቬሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ወስጥ ተከተው እና በሁለት ዶክመንት ላይ ስም እና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ግዥ/ ፋይናንስ አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- ጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከ10% በላይ የ ዋጋ ቅናሽ (Rebeat) የተደረገ ከሆነ ድርጅቱ በቀጥታ ከጨረታ ወድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- አሰሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መግቢያ እና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046 212 43 56
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ
