Tender Detail

Tender Details

  • Deadline10 Jan 2025, 10:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Equipment And Machinery

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ

የተተው  ዕቃዎች  ግልፅ  ጨረታ ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ቁጥር  ግ-37/2017

 

በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም

  • DIESEL GENERATOR,
  • SHOE OUTSOLE AND MOULD
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫ
  • PORTABLE CONTAINERIZED WAIST TREATMENT PLANT WITH ACCESSORY,
  • COFFEE GRINDER,
  • ANGLE IRON AND FLAT BAR,
  • MEMBRANE CLEANER እና የግንባታ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እና ከዋናው መስሪያ ቤት ገቢ ሂሳቦች ቡድን ሰነድ በመግዛት መመልከት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያይ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፣ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሸጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
  5. የግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ ፣የሞሉበት ሠነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ዋጋ 5% ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  6. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምር በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጐ በዚህ ዕለት ጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛወም በግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፤ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰበ የነበሩ ሰዎች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መሳተፍ አይችሉም ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ውድድር ማግልለ አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. የግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አሸናፊ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፣ በ5 (አምስት) ቀናት ወስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ /ያልተረከበ አንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተወወ ተቀጥሮ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናሉ።
  11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፣ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሽጦ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፤
  12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በገቢዎች  ሚኒስቴር  ጉምሩክ  ኮሚሽን  የሞጆ  ጉምሩክ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

 

Save Tender