የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢአጽ/ግንአዳ/007/2017
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (Furniture) ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ : ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረገጹ (website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ ፣ የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆነን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (cpo) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. 8፡30 ሰዓት በኢንተርፕራይዝ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 እንዲሁም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
