በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ አትክልትና ፍራፍሬ እና የተፈጥሮ ሀብት ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ፖሊታንት ቲዩብ፣ ጆርዲን እና ሎት 2 የአትክልት ዘሮችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ አትክልትና ፍራፍሬ እና የተፈጥሮ ሀብት ዳይሬክቶሬት አገልግሎት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ አትክልትና ፍራፍሬ እና የተፈጥሮ ሀብት ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውሉ
ሎት 1 ፖሊታንት ቲዩብ፣ ጆርዲን እና
ሎት 2 የአትክልት ዘሮችን ግዥ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን.
- በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የአትክልት ዘር ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ትከከለኛ ዘር ለመሆኑ ከሚመለከተው አካል የብቃት ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙ የፖሊታንት ቲዩብ፤ ጆርዲን እና የዘር ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት ገንዘብ የዋጋውን ጠቅላላ ድምር 1% /ፐርሰንት/ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ አሠርተው በቢሮው ስም ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳደሪያ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሲቀርብም ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱ ዋና እና ቅጅ በሚል ካልመጣ ከውድድር ውጭ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/058 320 8095 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ አትክልትና ፍራፍሬ እና የተፈጥሮ ሀብት ዳይሬክቶሬት አገልግሎት
