በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2017 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም Motor Cycle በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር በ2017 በጀት አመት በተያዘው ለመምሪያው አገልግሎት የሚውል የቋሚ ዕቃ ማለትም Motor Cycle በግልጽ ጨረታ በማውጣት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ ከ 24/4/2017 እስከ 8/5/2017 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 3,900 /ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን CPO /ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የቋሚ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ይቻላል፡፡
- ማንነት የበረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት ከ9/5/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል ነገር ግን የጨረታ ጊዜ የበዓል ቀን ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ውጪ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲገጥማችሁ አሰሪው መ/ቤት ጨረታ ካወጣው አካል ከጨረታው መክፈቻ እለት በፊት በስልክ ቁጥር 0333511042 / 0975429082 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ጨረታው ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታው ውድድር በጠቅላላ ዋጋ ሎት ድምር ነው።
- መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
