የአቃቂ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አቃቂ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 002/2017
የአቃቂ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም:-
- የደንብ ልብስ
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- ቋሚ ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:-
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር ከቢሮ ቀጥር 06 ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ የማይመለስ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 – 11፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በት/ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር ከቢሮ ቀጥር 04 ይከፈታል።
- ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በየሎቱ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑና የጨረታ ማስከበሪያው CPO ይወረስበታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4-71-57-50 መደወል ይችላሉ።
አድራሻ :- ከአቃቂ ንግድ ባንክ በግምት 100 ሜትር አለፍ ብሎ።
የአቃቂ የመንግስት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
