የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸዉ የተሽከርካሮች ጎማ Cori-7 Desk Top computer የቢሮ ጠረጴዛ ፤ ሜሽ ተሽከረካሪ ወንበር የእንግዳ ወንበር ከአቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡-
የቢሮ ዕቃና የመኪና ጎማ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BGO 03/2017
የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸዉ የተሽከርካሮች ጎማ Cori-7 Desk Top computer የቢሮ ጠረጴዛ ፤ ሜሽ ተሽከረካሪ ወንበር የእንግዳ ወንበር ከአቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡-
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች
- ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፤የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግስተ ተቋማት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ዉስጥ ስለመመዝገባቸዉ የሚገልጽ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተዉ የመንግስት ተቋም የተሰጠ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት ማስረጃ፤
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 20 መውሰድ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ የጨረታ ሰነዶቹን ዋናና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 20 ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ 125,400 (አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ አራት መቶ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል፤
- ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በቅድሚያ ያሲይዛሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ መወዳደሪያ ሃሳብ/ ዋጋ በመሙላት ዋና እና ቅጂውን ለየብቻ በኢንቨሎፕ አሽገዉ የድርጅታቸውን ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ማቅረብ አለባቸዉ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 251114709028 በመደወል መጠየቅ ይቻላሉ።
አድራሻ ፡- ሳሪስ አዲስ ጎማ ሆራይዘን ፋብሪካ ፊት ለፊት
ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ
ፊንፊኔ
