Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ህክምናና ላብራቶሪ ግቢ ውስጥ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 226 3095
  • Websitehttps://amharaforest.gov.et
  • Deadline11 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Equipment And Machinery

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋናው ጽ/ቤት የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double Hard Blade) ግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Forest Enterprise (የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ)


 

የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double Hard Blade)

ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አደኢ ግጨ - 005/2017

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋናው ጽ/ቤት የእንጨት መሰንጠቂያ ምላጭ (Double Hard Blade) ግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

    1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
    2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት ያላቸው፤
    3. ግዥው ከብር 200,000.00 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
    4. ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
    5. የተጋበዙ ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀንን ጨምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ በኢንተርፕራይዙ ዋናው ጽ/ቤት ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ገንዘብ ያዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
    6. ጨረታው በወጣ በ10ኛው ቀን ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ከሆነ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቅዳሜ ከሆነ ግን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
    7. 10ኛው ቀን እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
    8. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያ መሰረት በተገለፀው የስራ ቀናት የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በፖስታ በማሸማ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ ቢሮ ቁጥር 13 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
    9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋውን 2% CPO በኢንተርፕራይዙ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    10. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ማሳሰቢያ ፡- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቀበሌ 14 በአዴት መውጫ ከአዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ላቦራቶሪ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583202241 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender