በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ካፒታል በጀት በ2017 በጀት አመት በተያዘው የ Street light Maintenance በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት በኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ካፒታል በጀት በ2017 በጀት አመት በተያዘው የ Street light Maintenance በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በኤሌከትሮ መካኒካል ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የታደሰ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ኦርጅናል ማስረጃዎች እና ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመሄድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ሰዓት ድረስ ከ24/4/2017 እስከ 14/5/2017 ዓ/ም ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚሰሩ street light Maintenance ስራዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን / ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO /ሲ.ፒ.አ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 30,000 / ሰላሳ ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት 15/05/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፣ ነገር ግን የጨረታ መክፈቻው ጊዜ የበዓል ቀን ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታ ስነድ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡
- በስራ እና ስልጠና መምሪያ የተደራጁ ከሆነ የውል ማስከበሪያ፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና የቅድሚያ ክፍያ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲገጥማችሁ አሰሪዉ መ/ቤት ጨረታ ካወጣዉ አካል ከጨረታ መክፈቻ እለት በፊት በስልክ ቁጥር 0333511042 / 0975429082 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- በኮቪድ 19 ዙሪያ መካተት ያለበት
- ተጫራቾች ለፕሮጀክቶች ሰራተኞች በሙሉ የዕጅ መታጠቢያ ቦታ ማዘጋጀት የሚችል
- ተጫራቾች በስራው ለሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል፣ ሳኒታይዘርና አልኮል ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በተቻለ መጠን ሰራተኞች ርቀታቸውን ጠብቀዉ መስራት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚችል
- ተጫራቾች በኮቪድ - 19 ዙሪያ በሚደረጉ ጥንቃቄዎች የሰሩትን ስራ የሚገልፅ የአፈፃፀም ሪፖርት የክፍያ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ አብረው ማቅረብ የሚችል
- ጨረታው ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ ሆኖ መቅረብ የለበትም ከቀረበ ከጨረታ ዉጭ ይሆናል፡፡
- መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኮምቦልቻ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
