በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የላፕ ቶፕ ባትሪ፣ የላፕ-ቶፕ ቦርሳ ፣ የክስ ፋይል ፎልደሮች ላይ የሚለጠፉ ቁጥሮች፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና የሞተር ሳይክል ሄልሜት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የላፕ ቶፕ ባትሪ፣ የላፕ-ቶፕ ቦርሳ ፣ የክስ ፋይል ፎልደሮች ላይ የሚለጠፉ ቁጥሮች፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና የሞተር ሳይክል ሄልሜት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ፡-
- በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ /Specification/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ /CPO/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሥነ-ሥርዓቱን ኢያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 047 335 10 27/ 047 335 12 78
በደቡብ ም/ሕ/ክ/ መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ሚዛን አማን
