በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላለት ቀበሌዎች የውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 004/04/2017
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላለት ቀበሌዎች የውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፍቃድ ያሳደሳችሁ እና ከግብር ነጻ መሆናችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ
- በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበረያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO በጥሬ ብር ፣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው::
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይሀ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታውን ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከ23/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 23/2017 እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም።
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 /ስልሳ/ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0910106716 ወይም 0928011746 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጉንችሬ
