የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ሎት-1 የአፈር ማዳበሪያ የመጣባቸውን ባለ 50 ኪ/ግራም ከረጢቶች ፤ ሎት-2 ያገለገሉ የኬሚካል ጄሪካኖች እና ሎት-3 ያገለገሉ የአትክልት የውሃ ማጠጫ ጄሪካን፣ የውሃ ጄሪካን፣ ናብሳክ/የኬሚካል መርጫ/ እና የፕላስቲክ ሳፋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጣበስፋ/ያዕሽግጨ/09/2017
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
ሎት-1 የአፈር ማዳበሪያ የመጣባቸውን ባለ 50 ኪ/ግራም ከረጢቶች
ሎት-2 ያገለገሉ የኬሚካል ጄሪካኖች እና
ሎት-3 ያገለገሉ የአትክልት የውሃ ማጠጫ ጄሪካን፣ የውሃ ጄሪካን፣ ናብሳክ/የኬሚካል መርጫ/ እና የፕላስቲክ ሳፋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው ጥር 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 ላይ በተገለፀው አድራሻ ጥር 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000577307637 ገቢ በማድረግ ከታች በተመለከተው አድራሻ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከምሳ በኋላ ከ7፡00-11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00) መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ
ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5-586725/0912031748
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% /ሁለት ከመቶ/ በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.አ) ወይም ለ3 ወራት የሚያገለግል በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ) በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ አማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- በጨረታው ተሳትፎ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ከፋብሪካው ጋር ውል በመያዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሙሉ ክፍያ ቅድሚያ ከፍሎ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
