በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግስት በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የሚገኘው የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ርዝመቱ 12 ሜትር፣ ቁመቱ 2.50 የሆነና ስፋቱ 2.40 የሆኑትን የዕቃ ማመላለሻ ኮንቲነሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት
2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልላዊ መንግስት በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የሚገኘው የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ርዝመቱ 12 ሜትር፣ ቁመቱ 2.50 የሆነና ስፋቱ 2.40 የሆኑትን የዕቃ ማመላለሻ ኮንቲነሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ /ግለሰብ/ ከዚህ በታች ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በ2016 ዓ.ም ተጫራቹ በሚሰሩበት የስራ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ይህንን ማድረግ የማይችሉ ከሆነ ለዋስትና መያዣነት ያስዙት ገንዘብ ለልማት ማህበሩ ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በልማት ማህበሩ ስም በታወቀው ባንክ የተሰራ ሲፒአ ከኦሪጅናል ሠነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሠነዶችን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የሠነድ ገጽ ላይ ድርጅቱን የሚገልፅ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሠዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 400 /አራት ብር/ በመክፈል ከዳውሮ ልማት ማህበር ቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሠነዱ የጨረታው የቆይታ ጊዜ 15 ቀናት ካለቀ በኃላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታው ሰነድ አከፋፈት ሥነ- ሥርዓትን አያስተጓጓልም፡፡
- ጨረታው ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ካለ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጨማሪ ስለ ጨረታ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 047-3-45-02-58/ 09-17-83-23- 52/ 09-17-83-26-37 ይደውሉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
- የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓላት ወይም ሰንበት ላይ ከዋለ ለቀጣዩ የስራ ቀን የሚተላለፍ ይሆናል።
- ጨረታውን ያለፈው ድርጅት /ግለሰብ/ ኮንቴይነሩን ከቦታው ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ የሚያነሳ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የዳውሮ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት
