የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ሆኖ እነኚህን ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በባንክ የተረጋገጠ በሎት/Lot ሲሆን ሎት 1 ብር 7,100.00፣ ሎት 2 ብር 37,000.00፣ ሎት 3 ብር 38,000.00፣ ሎት 4 ብር 6,5000.00: ሎት 5 ብር 9,200.00፣ ሎት 6 ብር 78,000.00 እና ሎት 7 ብር 8,000.00 ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣ ለ15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ውኪሎቻቸው) በተገኙበት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናሻልና ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም የታሸገ ፖስታ በማድረግ አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር፡- 046-2-20-42-24/ 046-2-12-34-68 ይጠቀሙ፡፡
አድራሻ፡- አሮጌ ገበያ አለ በጅምላ ጎን
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
