የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሠራተኞች ሰርቪስ እና የመስክ መኪና አገልገሎት የሚውል መኪናዎች መከራየት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት
ሶስተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለሠራተኞች ሰርቪስ እና የመስክ መኪና አገልገሎት የሚውል መኪናዎች መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ሆነው እነኝህን ማስረጃዎች አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሎት 1 ብር 20,000.00፤ ሎት 2 ብር 15,000.00 እና ሎት 3 ብር 35,000.00 ለየብቻ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- የፒካፕ መኪና ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም የታሸገ ፖስታ በማድረግ አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 046-220-42-24/046-212-34-68 ይጠቀሙ::
አድራሻ፡- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
