Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Address መኮይ : የሰሜን ሸዋ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-444-0341
  • Website
  • Deadline14 Jan 2025, 9:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ፡-

ሎት 1 - የፅህፈት መሳሪያዎች                    ሎት 5 - ቋሚ የቢሮ እቃዎች

ሎት 2 - ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች                 ሎት 6 - ቋሚ ቢሮ አቃዎች/ፈርኒቸሮች

ሎት 3 - ሕትመቶች                              ሎት 7 - የህንፃ መሳሪያ እቃዎች

ሎት 4 - የፅዳት ዕቃዎች

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፤

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ወይም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 21/4/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ቀናት በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 የዕቃዎችን ዓይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1 እስከ 7 የተዘረዘሩትን የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን (ቫቱን) ጨምሮ 1.5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  7. በእያንዳንዱ ሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል። ሁሉም እቃዎች መሙላት አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በየሎቱ በመለየት በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 21/4/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 5/5/2017 ዓ/ም በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 1፡30 ሰዓት ማስገባት /ማቅረብ / ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛውቀን ማለትም 6/05/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በ3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም የጨረታ ሰነዳቸው ተሟልቶ ከቀረበ ባይገኙም በአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በይፋ ይከፈታል።
  10. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁትን ዕቃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  13. ፍርድ ቤቱ ካወጣው ጨረታ ውስጥ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033-444-0341/0030 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ወረዳ ፍርድ ቤት

መኮይ

 

Save Tender