Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara regio
  • Address , Phone: 058 332 09 939
  • Website
  • Deadline14 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara regio


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ10/2017

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የኤሌከትሮኒክስ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች፤

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  8. የጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡
  9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  11. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብከመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቀጥር 058 222 0814 መላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67/058 320 9939 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender