የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ዓይነት የወረቀት ህትመቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል::
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁ. ኢአጽ/ግንአዳ/005/2017
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ዓይነት የወረቀት ህትመቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል::
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
-
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ከድረ-ገጹ (Website) አትመው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣ የግብር መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ብር 350,000.00 (ሦስት መቶ ሐምሳ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ያላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጥር 09 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ማለትም ጥር 09 ቀን 2017 ዓ.ም በኢንተርፕራይዙ አገልግሎት ጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 217/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
