Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በንሳ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 046 337 0318
  • Website
  • Deadline13 Jan 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በንሳ ኤፍ ኤም 91.9 ማሰራጫ ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት በታቀደው የግዥ ዕቅድ መሠረት ለማሰራጫ ጣቢያ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እና ማሽነሪዎች፣ የቢሮ አላቂ ዕቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በንሳ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በንሳ ኤፍ ኤም 91.9 ማሰራጫ ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት በታቀደው የግዥ ዕቅድ መሠረት ለማሰራጫ ጣቢያ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እና ማሽነሪዎች፣ የቢሮ አላቂ ዕቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር በቀረቡት የመወዳደሪያ መስፈርቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሰነዶችን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታ ቀርበው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከበንሳ ሬዲዮ ጣቢያ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር-1 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ገንዘብ ከሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ሁለት ፐርሰንት ብር እውቅና ካለው ባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታው ሰነድ ተሟልቶ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከቶ በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማኖር ይህ ጨረታ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በበንሳ ራዲዮ ጣቢያ በግ/ክ/ን/አስ/ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁ.1 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ጊዜ ማለትም የቅሬታ ማቅረቢያ አምስት ቀናት በኋላ ካሸነፉት ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝና በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በጽ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ.1 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ ይሁንና 16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. አሸናፊ ድርጅቶች በተዋዋሉበት ውል ስምምነት መሠረት ያሸነፏቸውን ዕቃዎች በተጠየቀው ጥራትና ብዛት እስከ ጽ/ቤቱ ግቢ ድረስ በራሳቸው ወጪ ችለው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በንሳ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ

ስልክ ቁጥር ፡- 046 337 0318 / 09 10 61 48 30/09 26 12 20 62 / 0916 30 79 77

 

የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በንሳ ፌዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ

 

Save Tender