Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ከአያት አደባባይ ወደ ለሚኩራ ከ/ከተማ በሚወስደው መንገድ ካሊድ ሕንፃ ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 314 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116391163
  • Website
  • Deadline11 Jan 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባለቅ/መግዳ/2017/001

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ

ቅ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡-

ሎት- 1. የደንብ ልብስ       

ሎት- 2. ቋሚ ዕቃዎች

ሎት- 3. ለህንፃ ቁሳቁስ ዕድሳት ጥገና

ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር በዓመት ውል ገብቶ የሚያድስ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

    • ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት ካሊድ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አጠገብ በፋይናንስ ቡድን ክፍል ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት፡- ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል የ3,000 ብር (የሶስት ሺ ብር) CPO አሠርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ለሚኩራ ከ/ከተማ በሚወስደው መንገድ ካሊድ ሕንፃ ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 314 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116391163 /011-63-90-197/መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሚኩራ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender