ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሳሪስ /ሀኪም ማሞ/ የባህል ህክምና መውረጃ ላይ 100 ሜትር ወረድ ብሎ ሙሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የቡና ማደራጃ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ ኮንቴነር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ያገለገሉ ኮንቴነሮች ሽያጭ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሳሪስ /ሀኪም ማሞ/ የባህል ህክምና መውረጃ ላይ 100 ሜትር ወረድ ብሎ ሙሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የቡና ማደራጃ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ያገለገለ ኮንቴነር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ህጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት በሚገኘው መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛው ፎቅ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ፋይናንስ ግዥ ንብረት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቱን መጠን ለማወቅ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል መፈረም አለበት፡፡
- የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ጨረታው አ.አ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ግዢ/ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ ፡- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር:- 011-5-52-10-09/011-5-52-14-58/ ፖ.ሣ.ቁ 9515
ፋክስ፡- 011 551 3654
የአዲስ አበባ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
