Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Kombolcha Directive of Finance (የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ)
  • Address Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0913509999
  • Website
  • Deadline12 Jan 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት-1 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች፣ ሎት 02 የመኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara National Regional State Kombolcha Directive of Finance (የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ)


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት-1 ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የመኪና እቃዎች፣ ሎት 02 የመኪና ጎማ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 20 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል ከ19/4/2017 ዓ.ም እስከ 3/5/2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰአት 11፡30 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ገኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ19/4/2017 ዓ.ም እስከ 3/5/2017 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ 7 መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በ4/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በአል ከሆነና የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
  8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሠሪው መሥሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ቀን ከ 5/አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913509999 ወይም 0904662494 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመሥሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል፡፡
  13. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

 

Save Tender