Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ኮንሶ ፡ ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0945603600
  • Website
  • Deadline13 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Agriculture And Farming

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለካራት ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም -5 ተጠቃሚዎች የተለያዩ ዘር ግዥ እና የግብርና ቁሳቁስ/ፋብሪካ ውጤቶች ግዥ ለመፈፀም በመንግሥት የግዥ ደንብና መመሪያ መሠረት አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለካራት ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም -5 ተጠቃሚዎች የተለያዩ ዘር ግዥ እና የግብርና ቁሳቁስ/ፋብሪካ ውጤቶች ግዥ ለመፈፀም በመንግሥት የግዥ ደንብና መመሪያ መሠረት አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
  3. በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወርቀት ያላቸው
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ የሆኑ
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለአንዱ ሠነድ 300 / ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ለካራት ዙርያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ከፍለው ደረሰኝ በመያዝ ኮንሶ ዞን ካ/ዙ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ /ፋይናንሻል/ ሰነድ ኦርጅናል ለብቻ፣ ፋይናንሻል ኮፒውን ለብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል ለብቻ እና ቴከኒካል ኮፒውን ለብቻ በተለያየ ፖስታ አሽገው በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣አድራሻ ፣ስምና ፊርማ በማሳረፍ በ16ኛው የሥራ ቀን ካራት ዙርያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው 16ኛው የሥራ ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።

ማሳሰቢያ-

  • ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን የመንግስት መደበኛ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል።
  • በጨረታው መክፈቻ ዕለት ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ አለመሟላት የጨረታው አከፋፈት ሂደት አያስተጓጎልም።
  • በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት እሸናፊነቱ ተገልጾ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ዕቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዘው ለመቤታችን ማስረከብ ይኖርበታል።
  • አሸናፊው ከተለየ በኋላ እራሱን ከጨረታ የሚያገል ድርጅት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ አግባብ ባለው ህግ ይጠየቃል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ :- 0945603600/0916361663 ላይ መደወል ይችላሉ።

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

 

Save Tender