Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢስት ሳይድ ቪላ እና የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤቶች ማኀበር
  • Address ኢትዯጵያ, Phone: 0911843521
  • Website
  • Deadline02 Jan 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water System Installation

ኢስት ሳይድ ቪላ እና የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤቶች ማኀበር በማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስቆፍረው የከርሰ-ምድር ውሃ የቁፋሮና የፓንፕ ተከላ ሥራ የሚያከናውን በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊና ሰፊ-ልምድ ያለውን ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

ኢስት ሳይድ ቪላ እና የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤቶች ማኀበር


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢስት ሳይድ ቪላ እና የጋራ ህንፃ ቤት ባለቤቶች ማኀበር በማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስቆፍረው የከርሰ-ምድር ውሃ የቁፋሮና የፓንፕ ተከላ ሥራ የሚያከናውን በዘርፉ የተሰማራ ህጋዊና ሰፊ-ልምድ ያለውን ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራች ድርጅቶች ከዚህ በታች የተሰዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

  1. የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የከርሰ-ምድር ውሃ ቁፋሮ ስራ አከናውነው ያስረከቧቸውንና አሁን ይህንን ስራ እየሰሩላቸው ያሉ ድርጅቶች ካሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  4. የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤
  5. የአፈር ምርምርና አካባቢያዊ ጥናቶችን ኮፒዎች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን እስከ ታኅሣሥ 24/2017 ዓ.ም ድረስ ለማህበሩ ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው።

ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

     ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ፡- 0911843521መደወል ትችላላችሁ::

 

Save Tender