የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራ ህትመት ግዥ ለመፈጽም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራ ህትመት ግዥ ለመፈጽም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ሣጥን የሚታሸግበት ቀንን ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
የግዥ መለያ ቁጥር |
|
1 |
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራ ህትመት ግዥ |
ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት |
RE-DBE/NCB/ PR/001/2024/25 |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን
|
ተ.ቁ |
ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|
1 |
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባንዲራ ህትመት ግዥ |
10,000.00 በሲ.ፒ.ኦ. (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ህጋዊ ከሆነ ባንክ |
- ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶችን ያቀርባሉ፡
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /T.I.N/
- የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ የጽሁፍ የጽሁፍ ማስረጃ (ጊዜው ያላለፈበት መሆን ይኖርበታል)
- የተ.እ.ታክስ /VAT/ ሰርተፊኬት
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር/ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ታወር ሁለት በባንኩ እግረኛ መግቢያ ክፍያውን ፈጽመው በባንኩ ታወር ሶስት 1ኛ ፎቅ ከግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ ለተጫራቾች መሸጥ የሚጀምረው ከታኅሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒካልና የዋጋ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ በሰንጠረዥ እስከ ተገለፀው ቀን እና ሰዓት ድረስ በባንኩ ታወር ሶስት አንደኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሽግ ማስገባት ይችላሉ::
- አሸናፊው ተጫራች በተፈለገው ጥራት መሠረት ስራውን ካላከናወነ ባንኩ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ በመሆኑ ተጫራቾች ይህንን ከግንዛቤ አስገብተው ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ናሙናዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- የጨረታ ሰነዱ ቋንቋ አማርኛ ነው:: ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ታወር ሶስት 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ ዳይሬክቶሬት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0115578088 የውስጥ መስመር 364 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
