Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ
  • Address ቀበሌ-13 ሆምላንድ ሆቴል ፊት ለፊት አብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ህንፃ ውስጥ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251-582203860
  • Website
  • Deadline08 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎችን አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ


ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር እቃዎችን አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-9 የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒውን ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ግቢ ውስጥ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይታሽግና 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአብክመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር (+251)-5-82-20-38-60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፡-  ቀበሌ-13 ሆምላንድ ሆቴል ፊት ለፊት አብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ህንፃ ውስጥ

 

በአማራ ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የመንግስት  ኮሙዩኒኬሽን  ቢሮ

 

Save Tender