የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የግንባታ ግብአት ጥራት መፈተሻ የላብራቶሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
South Nation Nationality of Peoples Regional State Construction Autority (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የግንባታ ግብአት ጥራት መፈተሻ የላብራቶሪ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ፣ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- በገቢዎች ባለስልጣን የምዝገባ ሠርተፊኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአካል በመቅረብ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአስራ አምስተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስh 6:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በ8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመስከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ቴክኒካል አሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታ ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ዋጋ መሙያ ብቻ መጠቀም አለባቸው።
ስልክ ቁጥር ፡- 0461810701
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
