በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለሐኪም ግዛው ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የኦክስጅን ሙሌት (Medical Oxygen filling) አገልግሎት ለሁለት ዓመት የማዕቀፍ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Debre Berhan University (ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DBU/AWHSC/02/2017
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለሐኪም ግዛው ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የኦክስጅን ሙሌት (Medical Oxygen filling) አገልግሎት ለሁለት ዓመት የማዕቀፍ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ -
- ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃና ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና ወይም የክፍያ ማዘዣ CPO እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000655215054 ገቢ በማድረግና በካምፓሱ ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር F1-03 ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማህተም በማስደረግ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-01 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ (Original and copy) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-01 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ጠዋት 4፡30 ላይ የዋጋ ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፤ ከስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና እና ከውስጥ ኦዲት ሥራ አስፈጻሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት በካምፓሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ዕለቱ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሱት ቀናትና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ትክከለኛውን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ እንገልፃለን፡፡ የዋጋ ሰነድ ግምገማ እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ለሁሉም ተጫራቾች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን የህክምና ኦክስጅን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሐኪም ግዛው ሆስፒታል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ድርጅቶች በስልክና በደብዳቤ እንዲሁም በካምፓሱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩት ሰነድ ላይ ዘወትር በሥራ ሰዓት የሚሠሩ ስልኮችን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
