በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል አሪ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በአሪ ዞን ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ላይ የማህበረሰብ ፋርማሲና ስቶር ግንባታ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል አሪ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በአሪ ዞን ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ላይ የማህበረሰብ ፋርማሲና ስቶር ግንባታ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ፡-
- በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ GC/BC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግንባታ ተቋራጭ፣
- በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተመዝግቦ ለ2017 ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሰረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፣
- ለ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቂጥር ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ለ2017 ዓ/ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ /2017 ዓ/ም/ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት የያዘ፣
- በክልሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣
- ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረክብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል፣ ማዘግየት፣ ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈጻጸም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማንኛውም የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀክቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቅያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቅያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ፤ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 የስራ ቀናት ውስጥ ከአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ በጨረታው በመሳተፍ መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ እና በማሸግ ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 22ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኃላ ፋይናንሽያል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /CPO/ 20,000 ብር ነው፡፡
- ተጫራቾች በግንባታው ስፍራ በመገኘት የሳይት ምልክታ በማድረግና ከአሰሪው መ/ቤት የሳይት ምልከታ ማረጋገጫ በመውሰድ ከመጫረቻ ሰነዱ ቴክኒካል ሠነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማሳሰቢያ :- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- +251-916-13-59-77 ወይም +251-9-26-10-41-34 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ጂንካ
