በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ የቢሮ ግብአቶችን በሎት ከፋፍሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Regional State Health Bureau (በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ የቢሮ ግብአቶችን በሎት ከፋፍሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ሎት
|
ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት እና ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
ምርመራ |
|
1 |
የጽሕፈት መሳሪያዎች |
ሎት 1 |
ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ በ8፡30 ይከፈታል። |
በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዝርዝር መረጃውን በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመለክቱ |
|
2 |
የጽዳት ዕቃዎች |
ሎት 2 |
||
|
3 |
የሰራተኞች ደንብ ልብስ |
ሎት 3 |
በመሆኑም ተጫራቾች
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 /አምሳ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በክልሉ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋና ዶክመንታቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ጨምሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያውን ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በቢሮው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ውል የሚፈጽም ሲሆን ያሽነፈውን ዕቃ /ንብረት/ ከክልል ጤና ቢሮ ወራቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- በስልክ ቁጥር ፡- 046 32 69 229
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ
ወራቤ
