Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ወሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0902691555
  • Website
  • Deadline07 Jan 2025, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደጎሎ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለደጎሎ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የግዥ መጠን ከብር 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ በቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፤
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ ከጨረታው ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን አውቀው በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የስራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዳቸው ሎቶች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፤
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመ/ሂ 1 ማስያዝ ያለባቸውና የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ስፔስፊኬሽን መሠረት አሸነፉባቸው ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና በማቅረብ ውል መውሰድ አለባቸው፤
  11. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፍ/ን አስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  12. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛውን ቀን 3፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን እና ካሉት የስራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
  13. መ/ቤቱ በጨረታው የሚገዙ እቃዎች ላይ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
  15. ማንኛውም ተጫራች ግዥው በጥቅል (በሎት) የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝር ዕቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል። የተዘረዘሩትን እቃዎች በሙሉ ለእያንዳንዳቸው እቃ ያለ መሙላት ከጨረታው ውድቅ የሚያስደርግ ሲሆን አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ገቢ አድርገው ሳያጠናቅቁ ክፍያ የማይፈፀም መሆኑን እና በውለታው መሠረት ዕቃውን ጨርሰው ለመ/ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፤
  16. እያንዳንዱ ተጫራች ጨረታውን መሙላት ያለበት ከታክስ ጋር ነው። ከታክስ ጋር ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ያስደርጋል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  18. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0902691555/0920203135 ላይ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደጎሎ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender