Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት ከባሮክ ሆቴል አጠገብ ወይም በተለምዶ ጋሪ ተራ ተብሎ ከሚታወቀው ቦታ ፊት ለፊት : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0113658115
  • Website
  • Deadline06 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ያገለገሉ እና ያላገለገሉ (ስራ ላይ ያልዋሉ ትርፍ የሆኑ) እቃዎችን በሽያጭ ማስወገድ ይፈልጋል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት


የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ያገለገሉ እና ያላገለገሉ (ስራ ላይ ያልዋሉ ትርፍ የሆኑ) እቃዎችን በሽያጭ ማስወገድ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል የፋይናንስ ቢሮ ወይም በዞን ፋይናንስ መምሪያ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ በውሃ አገልግሎት ድርጅት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ CPO ጥቅል ንብረቱ ለመግዛት የሚሞሉትን ዋጋ 10% በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ተወዳዳሪ የሚለየው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ ነጠላ እቃ ባቀረቡት ዋጋ መሰረት የቀረበ ከፍተኛ ዋጋ ወይም በጥቅል ዋጋ በተሻለው የጨረታ አሸናፊ የመለየት ስራ ሊሰራ ይችላል፡፡
  • ማሳሰቢያ :-  ፅ/ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት እያስተጓጉልም፡፡
  • መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
  • የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም እቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  • የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ የህዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  • የንብረቶቹን አይነት እና ጥራት በአካል በመቅረብ ማየት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ :- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ድርጅት ከባሮክ ሆቴል አጠገብ ወይም በተለምዶ ጋሪ ተራ ተብሎ ከሚታወቀው ቦታ ፊት ለፊት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ በአካል

በመቅረብ ወይም

በስልክ ቁጥር :- 0113658115/0913159503/ ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

ጉራጌ  ዞን  የወልቂጤ  ከተማ  አስተዳደር  ውሃ  አገልግሎት  ድርጅት

Save Tender