Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን
  • Address በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ግዥ ንብረት ቢሮ ቁጥር 309 ሦስተኛ ፎቅ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 096 768 4656
  • Website
  • Deadline01 Jan 2025, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን


በድጋሚ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር  02, 2017

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ፡-

  1. 2017 ዓ/ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ ትችል
  2. አግባብ ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ሴርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና ተጨማሪ ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በህጋዊ ተጫራቾች ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብቶው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. ተጫራቾች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደርያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቅ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  5. አንድ ተጫራች ከአንድ ሠነድ በላይ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር (100,000) አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ወይም የክፍያ ማስያዣ (Cpo) ከማረጋገጫ ሠነድ ጋር ማቅረብ ሚችል/ትችል፡፡
  7. ተጫራቾች በመመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገበበት ሰርትፊኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአሥር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ግዥ ፋይናንስና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 40 በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታው ሠነድ ተጫራቾች በመመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ መስከበሪያ (BID BOND) ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናልና ቴክኒካል ሁለት ኮፒ ሠነዱ በተለያዬ በፖስታና ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በመጨመር በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (11ኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 - 4፡30 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት 4፡30 ይታሸጋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ የዚያኑለት 5፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገላፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. ገዥ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ ተጠበቀ ነው፡፡

 

የሲዳማ  ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  ፖሊስ  ኮሚሽን

 

Save Tender