የአማራ ከልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2017 በጀት አመት ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን በመደበኛ በጀት፤ በተራዶኦ በጀት እና ከውስጥ ገቢ በጀት ለመግዛት 1ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ 2ኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 3ኛ የፅዳት እቃዎች ፣ 4ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና የመኪና ጎማ ፣ 5ኛ የህክምና ላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች ፣ 6ኛ ላቦራቶሪ የህክምና መሳሪያዎች ፣ 7ኛ የግንባታ እቃዎች ፣ 8ኛ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ የእጅ ዋጋ አገልግሎቶችን በአገር አቀፍ ሰፊ ተነባቢ ባለው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 001/2017
የአማራ ከልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ በ2017 በጀት አመት ለኢንስቲትዩቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን በመደበኛ በጀት፤ በተራዶኦ በጀት እና ከውስጥ ገቢ በጀት ለመግዛት 1ኛ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ 2ኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 3ኛ የፅዳት እቃዎች ፣ 4ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና የመኪና ጎማ ፣ 5ኛ የህክምና ላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች ፣ 6ኛ ላቦራቶሪ የህክምና መሳሪያዎች ፣ 7ኛ የግንባታ እቃዎች ፣ 8ኛ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ የእጅ ዋጋ አገልግሎቶችን በአገር አቀፍ ሰፊ ተነባቢ ባለው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዟል፡፡
- በየዘርፉ አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ማቅረብ የሚችል
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢነት የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የመፀዳጃ ቤት ግንባታ የእጅ ዋጋ ከደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ BC, GC የግንባታ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተዘረዘሩትን መስፈርቶ መስፈርቶት የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን ወይም ዝርዝር መገለጫ ጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ዩቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት መሳተፍ ይቻላል።
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሸጥበትን ዋጋ በትክከል በመሙላት በጠቅላላ ከሞሉት ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማሰብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ከመፀዳጃ ቤት ግንባታ የእጅ ዋጋ ውጭ የሆናችሁ ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ አማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን የግዥ አይነት በፖስታ ላይ በመግለፅ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ቁጥር- 033 311 52 20 ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ለመፀዳጃ ቤት ግንባታ የእጅ ዋጋ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ አማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን የግዥ አይነት በፖስታ ላይ በመግለፅ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ደሴ ቅርንጫፍ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝባዊ በዓል /ቅዳሜ/ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት በሚል የንግድ ፍቃድ የሚወዳደር ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የንግድ ፍቃድ ላይ የንግድ አይነት ዝርዝር መገለፅ ይኖርበታል ይህ ካልሆነ መወዳደር አይችሉም።
- ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሚያቀርበው ቋሚ እቃዎች ላይ የ6 ወር ጋራንቲ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከተው ባለሙያ እየተረጋገጠ በመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታ አሸናፊ ከለየ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት መ/ቤቱ የሚገዛውን የእቃ ብዛት 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት ይኖረዋል።
- የጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩት በነጠላ ዋጋ ይሆናል።
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ያንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ፣ ፊርማ ፣ አድራሻ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ደሴ ቅርንጫፍ
