Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ ክ/ከ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው በልደታ ፍርድ ቤት ወደ አብነት በሚወስደው መንገድ ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ጎን, Phone: 0118494257
  • Website
  • Deadline01 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicles Rent

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ ክ/ከ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የቋሚ አላቂ፣ ቋሚ እቃ፣ ህትመት፣ ድንኳን ኪራይ ፣ መድረክ ማስዋብ እና ትራንስፖርት ማጓጓዣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ ክ/ከ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት


የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ  የጨረታ  ቁጥር  001/2017

 

በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ ክ/ከ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የቋሚ አላቂ፣ ቋሚ እቃ፣ ህትመት፣ ድንኳን ኪራይ ፣ መድረክ ማስዋብ እና ትራንስፖርት ማጓጓዣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል።

በዚሁ መሰረት ፡-

  1. የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የቋሚ አላቂ፣ ቋሚ እቃ፣ ህትመት፣ ድንኳን ኪራይ ፣መድረክ ማስዋብ ፣ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ማጓጓዣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የፅህፈት መሳሪያ 1% ፣ የፅዳት ዕቃ 1%፣ የቋሚ አላቂ 1%፣ ቋሚ እቃ 1%፣ ህትመት 1%፣ ድንኳን ኪራይ 2% ፣ መድረክ ማስዋብ 2% ፣ ትራንስፖርት መኪና ኪራይ 2% እና ማጓጓዣ የመኪና ኪራይ 2% አገልግሎት ግዥ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የልደታ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጽ/ቤታችን በአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ቅ/ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአስተዳደር እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  5. ጨረታው በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ኦርጅናል እና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፡፡

አድራሻ ፡-  ልደታ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው በልደታ ፍርድ ቤት ወደ አብነት በሚወስደው መንገድ ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ጎን ሲሆን ለበለጠመረጃ በስ.ቁ. 0118494257 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

 

በአዲስ  አበባ  መሬት  ልማትና  አስተዳደር  ቢሮ  የልደታ  ክ/ከ  መሬት  ልማትና  አስተዳደር  ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender