በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ል/ክ/ከ/ወ/10/ፋ/ጽ/ቤት
የግዥው መለያ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዥ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
የሎት ምድብ የጨረታ ማስከበሪያ CPO
ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ 15,000.00
ሎት2. ፈርኒቸር እቃ ግዥ 15,000.00
በዚሁም መሰረት ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች 2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ ህጋዊ የቲን ነምበር እና የቫት፤ ክሪላስ ያላችሁ ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው ባለስልጣን ደብዳቤ የሚያመጡት የጨረታ ሰነድ በነጻ መውሰድና 3% ቅናሽ የሚደረግላቸው እራሳቸው ላመረቱት እቃና ቫሊው አድ ላደረጉት እቃ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት እንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት በወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው ቀን 11፡30 ጨረታው ያልቃል፡፡ አልቆ የሚታሸግ ሲሆን በ11ኛው ቀን 2፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩበት ሎት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ እና ሳምፕል ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ለእያንዳንዱ ዋጋ ከቫት ጋር ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤት እስከ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ ካለዎት፡-
- ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115574351 በመደወል ወይም ቅ/ልደታ ቤ/ክ ጀርባ አዲስ አበባ ፎምና ፕላስቲክ ፋብሪካ አጠጉበ ቢሮአችን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
