በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክ/ መንግሥት የከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የቀረቡ የግንባታ ሥራዎችን በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውን የንግድ ድርጅቶች /ተቋራጮች/ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 005/2017
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክ/ መንግሥት የከፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የቀረቡ የግንባታ ሥራዎችን በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸውን የንግድ ድርጅቶች /ተቋራጮች/ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ መሣተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች በሎት ለተዘረዘሩ ግንባታ ሥራዎች ማለትም፡-
ሎት.01 በሺሾ እንዴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም ድጋፍ በቡታ ሆራ እና በዲንቢራ ጤና ጣቢያ የእንግዴልጅ መቅበሪያ ግንባታ
ሎት.02 በሺሾ እንዴ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም ድጋፍ በዋረታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገነባው የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ ግንባታ፤ ሲሆን ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የታደሰ የደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግንባታ ሥራ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣
- በመንግሥት መ/ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገበ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ ሁለት ሁለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኮፒ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም መረጃ እና የምርጥ ተሞከሮ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (ለሎት 01፣ የብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር / CPO ለሎት 02 የብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/ CPO በሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ስም አሠርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሣ/ ብር ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5 ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር የተከለከለ ነው::
ጨረታው በ22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች / ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመከፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይሆናል ፣
ማሳሰቢያ መ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0476680200 መጠየቅ ይችላሉ።
የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
ሺሺንዳ
