Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Chemicals And Reagents

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የሲቲ ስካን፣ የኤም አር አይ እና የዳይሌሲስ ሪኤጀንቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የሲቲ ስካን፣ የኤም አር አይ እና የዳይሌሲስ ሪኤጀንቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ስለ ሪኤጀንቶች የሚገልጸውን ዝርዝር ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

  1. ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድሃኒት ባለስልጣን የታደሰ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው ።
  3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15,000 በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በ15 ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር  0463299270  ደውሎ  መጠየቅ  ይችላሉ።

 

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ  ስፔሻላይዝድ  ሆስፒታል

 

Save Tender