Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሎጅስቲክስና ፋይናንስ አስ/ዋና ክፍል
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 011-6-81-30-00
  • Website
  • Deadline01 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለደ/ብርሃን ከተማ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና በሰ/ሸ/ዞ/ፓ አድማ መከላከል ፖሊስ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ ቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌከትሪክ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸርና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሎጅስቲክስና ፋይናንስ አስ/ዋና ክፍል


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

   የጨረታ  ቁጥር :- 412/ሎ/ፋ/አ/31/8

 

በአማራ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለደ/ብርሃን ከተማ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና በሰ/ሸ/ዞ/ፓ አድማ መከላከል ፖሊስ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ ቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌከትሪክ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸርና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. የግብር ከፋይ (TIN) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 60 /ስልሳ ብር/ በመክፈል ከሎ/ፋ/አስ/ዋ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰ/ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በሎ/ፋ/አስ/ዋ/ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 23/4/2017 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሎ/ፋ/አስ/ዋ/ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በ23/4/2017 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 011-6-81-30-00 በስልክ ቁጥር 011-6-81-62-06 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. መ/ቤቱ በነጠላ ሆነ በሎት /በጥቅል/ ዋጋ ማወዳደር ይችላል፡፡
  13. የተጠየቁትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

 

በአብክመ  ፖሊስ  ኮሚሽን  የሰሜን  ሸዋ  ዞን  ፖሊስ  መምሪያ  ሎጅስቲክስና  ፋይናንስ  አስ/ ዋና  ክፍል

Save Tender