Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤት ምድር ኃይል ግቢ የሚገኙትን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የተለያዩ  ቁርጥራጭ  ብረታ  ብረቶች  (ስክራፕ)

ሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤት ምድር ኃይል ግቢ የሚገኙትን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስክራፕ) ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስክራፕ) ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 20% /Ministry of Defense Property Sales Saving Account/ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ንብረት ሽያጭ ማጠራቀሚያ ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ባሉት ቀናቶች የሚሸጡትን ብረታ ብረቶች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ጦር ኃይሎች ፊትለፊት ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ መመልከት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች ከጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ከ/ከተማ፤ ወረዳ፣ የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን በግልጽ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  6. ጨረታው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምድር ኃይል ግቢ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ብረታ ብረቱን በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ብረታ ብረቶቹን ከቦታው ለማንሳት የሚያስፈልግ ማንኛውንም ወጪ ሙሉ በሙሉ በገዢዎች ይሸፈናል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ አድራሻ አዲስ አበባ ምድር ኃይል ግቢ መከላከያ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር 0113-72-28-60 መደወል ይቻላል።

 

ሀገር  መከላከያ  ሚኒስቴር

Save Tender