ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀከት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Chemical Industry Corporation (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኬ.ኢ.ኮ/ግ/ጨ/06-2017
ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ፤
ሎት1 የተለያዩ ዕቃዎች (የጎማ ዛፍ ወተት መሰብሰቢያ አሸንዳ፣ ወተት መሰብሰቢያ ካቶራ፣ የወተት መቀበያ ሳህን፣ የእጅ ባትሪ ቀፎ፣ ትልቁ ባትሪ ድንጋይ፣ የፕላስቲክ ባልዲ፤ ፕላስቲክ በርሜል፣ የምርት ማሸጊያ ፕላስቲክ፣ ሀንገር ሽቦ፣ የምርት ማሸጊያ ባዶ ማዳበሪያ፣ ገጀራ፣ ፕላስቲክ ሳፋ ፣ ሜትሮ ላክ እና ሞረድ)
ሎት2 ኬሚካሎች (ፀረ አረም ኬሚካል፣ አሞኒያ እና ፎርሚክ አሲድ) እና የኬሚካል መርጫ መሳሪያን እንዲሁም ለዋና መ/ቤት አገልግሎት የሚውል
ሎት3 ዲጂታል ካሜራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (tax clearance) የግብር ከፋይ፣ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር አንድ መቶ አምሳ (ብር 150.00) በመክፈል ቦሌ አካባቢ ፍሬንድ ሺፕ ህንፃ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ የኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ስላሳ (30) ቀናት በአየር ላይ ይውላል፣ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች ያዘጋጁትን የጨረታ ሠነድ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ኦፕሬሽን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ባለው የሥራ ቀናት ከጧቱ 2፡00 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ይሆናል። የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ መወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለም። 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋል።
- ጨረታው በተዘጋበት ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሪጅናል እና ኮፒ ለይተው በተለያየ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኬሚካል ኢንዲስትሪ ኮርፖሬሽን ስም ለጨረታ ያቀረቡትን ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በባንክ ሲፒአ ወይም በቅድሚያ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒክ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለበለጠ መረጃ 011-6-62-90-15/011-6-15-14-68
የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
