Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Printing And Publishing

ተቋማችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ጎማ ፣ የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ህትመት እና አመታዊ ጥቅል ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

     የጨረታ  ቁጥር  ኢኤአ /ፍፋግ/ግጨ-010/2017

 

ተቋማችን የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ ጎማ ፣ የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ህትመት እና አመታዊ ጥቅል ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ሎት

የዕቃው  ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1

የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪ ጎማ

300,000.00

 

ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

2

የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ህትመት

500,000.00

 

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

3

አመታዊ ጥቅል ህትመት

150,000.00

 

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንከ 10ኛ ፎቅ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. አድራሻ፡- ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንከ ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በስልክ ቁጥር 011-126-66- 05/011-156-01-48 ይደውሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <<ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY>> በሚል መሆን ይኖርበታል፤
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ  አገልግሎት

 

Save Tender