Tender Detail

Tender Details

  • Company Synergy PLC Ethiopia (ሲነርጂ አክሽን ፎር ኢትዮጵያ)
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0911122087
  • Website
  • Deadline25 Dec 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

ሲነርጂ አክሽን ፎር ኢትዮጵያ (Synergy Action for Ethiopia (SAFE)) አዲስ ሞተር ሳይክል (Star HCK 150 CC Motor bike) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Synergy PLC Ethiopia (ሲነርጂ አክሽን ፎር ኢትዮጵያ)


የጨረታ  ማስታወቂያ

 

ሲነርጂ አክሽን ፎር ኢትዮጵያ (Synergy Action for Ethiopia (SAFE)) አዲስ ሞተር ሳይክል (Star HCK 150 CC Motor bike) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም:-

  1. ሞተር ሳይከሉን ማየት የምፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) የስራ ቀናት ውስጥ በስልክ ቁጥር 0912494636 በመደወልና ቀጠሮ በመያዝ ማየት ይቻላል፣
  2. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ማቅረብ አለባቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስ የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር አለባቸው፣
  4. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሦስት (3) የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስገባው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አይመለሰለትም፡፡ ለሌሎች ተጫራቾች ግን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘባቸው ይመለስላቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋና የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ (CPO) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በደብረ ማርቆስ ከተማ፣ ተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ፣ ጉዱ ካሳ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 62 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፣
  6. የጨረታው አሸናፊ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ12ኛው የስራ ቀን ለአሸናፊው ይገለፃል፣
  7. እንዲከፈሉ በህግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል፣
  8. የስም ዝውውር የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ገዢው/ አሸናፊው ይከፍላል፣
  9. ሲነርጂ አከሽን ፎር ኢትዮጵያ ሞተር ሳይክሉ በገዢው ስም እንዲዘዋወር ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማረጋገጫ ይሰጣል/ ያቀርባል እና
  10. ሲነርጂ አክሽን ፎር ኢትዮጵያ ሞተር ሳይክሉን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911122087/ 0961250860/0912494636 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ሲነርጂ  አክሽን  ፎር  ኢትዮጵያ

Save Tender