በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ወጪ የሚውል ከአለም ባንከ በተገኘ በጀት ድጋፍ ጋፍ ኖራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 184/17
የሀገሪቱ /የክልሉ ስም፡- ኢትዮጵያ/ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
የፕሮጀክቱ ስም፡- የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀከት
የፕሮጀክቱ ቁጥር፡- P178566
የብድር ቁጥር፡- 7156-ET
የግዥው አይነት፡- የኖራ ግዥ
የግዥ መለያ ቁጥር :- ET-SER-FSRP-437162-GO-RFB
- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ለምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ወጪ የሚውል ከአለም ባንከ በተገኘ በጀት ድጋፍ ጋፍ ኖራ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ 16,209 ኩንታል ኖራ ለመግዛት ብቁ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡ ስለሆነም በጨረታ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ከ07/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እየመጣችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ክፍያው የሚፈጸመው በጥሬ ገንዘብ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 80,000.00 /ሰማንያ ሺህ ብር/ ብቻ በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች እስከ 06/05/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው ስለሚከፈት የአከፋፈት ስነ-ስርዓት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መንግስት በ06/05/2017 ዓ.ም ጠዋት በ4፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የቢሮ አድራሻ ፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መንግስት ግብርና ቢሮ ወደ ዲላ ዩኒቨርስቲ መሄጃ መንገድ፣ የዲላ መምህራን ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ቅጥ ግቢ ውስጥ
ስልክ ቁጥር ፡- 046-1-31-01-34
ዲላ፤ ኢትዮጵያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
