Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0462121127
  • Website
  • Deadline30 Dec 2024, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Pumps, Motors And Compressors

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


የግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

         1. ሎት አንድ ኤሌክትሮኒክስ

         2. ሎት ሁለት የውሃ ፓምፕ

በዚሁ  መሠረት

  • በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  • የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
  • የተጨማሪ እሴት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶኮፒ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ በA4 ወረቀት ለአንድ ወረቀት አንድ ኮፒ ብቻ በማድረግና በማዘጋጀት እያንዳንዱን በተናጠል በፖስታ ማሽን በፖስታው ውጭ የሰነዱን ዓይነት አሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመፃፍ ሁሉንም በአንድ አናት ፖስታ በማሽን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።

ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር ብቻ) CPOን ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ (Specifeation) ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/ ዳይሬከቶሬት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ከፈለው በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ በድርጅቱ በዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያተተ ስለመሆኑ በመግለፅ ፖስታን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለግዥ ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እንዲያስገቡ እያሳሰብን ጨረታው 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ ፡  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ሲዳማ  ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  ፋይናንስ  ቢሮ 

 

Save Tender